የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የብሬል ህትመት ዉጤቶችን ለኢትዮጵያ ዓይነ ሥዉራን ብሔራዊ ማህበር አስረከበ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትኩረት እየሠራባቸዉ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ዜጎች ስለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና የምርጫ ሂደት በቂ መረጃ እና ግንዛቤ የሚያገኙበትን አካታች ስልት መቀየስ እና የተለያዩ መገናገኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሥነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት መስጠት ዋነኛዉ ተግባር ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት የቦርዱ የሥነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ሥራ ክፍል ዓይነ-ሥዉራን ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ አምስት የተለያዩ ጉዳዮችን የያዙ ማለትም፤ የምርጫ ሒደት፣ ምርጫ በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት የምርጫ ሥርዓት ትከተላለች፣ ሰላማዊ ምርጫ በኢትዮጵያ፣ እና ዴሞክራሲ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚል አርዕስት በብሬል የተዘጋጁ 100 ብሮሸሮችን ለኢትዮጵያ ዓይነ ሥዉራን ብሔራዊ ማህበር አስረክቧል፡፡