የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሬይል የተዘጋጁ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችን ለኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሓፍት አገልግሎት አስረከበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምርጫ ጋር ተያያዥነት ባላቸው በአምስት የተለያዩ አርእስቶች የተከፋፈሉ የብሬይል ብሮሸሮችንና ዐዋጆችን ለኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. አስረከበ። በብሬይል ከተዘጋጁት ኅትመቶች ውስጥ ዴሞክራሲ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ አካታች የሆነ የምርጫ ሂደት፣ ምርጫ በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት እና ሰላማዊ ምርጫ በኢትዮጵያ የሚሉ አርእስቶች ይገኙበታል። ቦርዱ በተጨማሪም በብሬይል የተዘጋጀ ‘የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011’ን ለአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አበርክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ የሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍሉ አማካኝነት ከምርጫ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችንና ዐዋጆችን ለተለያዩ የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት መስጫ ተቋማት በማበርከት ዜጎች ስለምርጫ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል።