የምርጫ ቦርድ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች ቀሪና የድጋሚ ምርጫ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ምርጫ በሚያደርግባቸው አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች እና ለመረጃ መለዋወጥ እንዲያገለግል ጊዜያዊ የጥሪ ማዕከል አቋቁማል ስለሆነም ከ6ኛው ዙር ሀገራዊ ቀሪና የድጋሚ ምርጫ ጋር በተያያዘ መረጃ ለማግኘት፤መረጃ ለመስጠት እና አስፈላጊ የሆኑ ጥቆማዎችን ለምርጫ ቦርድ ለማቅረብ የሚከተሉትን ነፃ የስልክ መስመሮች ይጠቀሙ፡
- 665 ከቦርዱ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሚመጡ ማንኛውም ጥያቄዎች የሚስተናገድበት የውስጥ መረጃ መቀበያ መስመር ነው፡፡
- 778 ደግሞ ለህዝብ ይፋ የሆነ ሰዎች ወደ ምርጫ ቦርድ በመደወል ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት፤ጥቆማቸውን የሚሰጡበት እና ሀሳባቸውን የሚገልፁበት መስመር ነው፡፡
ቁጥሮቹ ለደዋዮቹ ነፃ የስልክ መስመሮች ስለሆኑ እና ሁሉንም የስልክ ጥሪ ክፍያዎች የሚከፍለው የምርጫ ቦርድ ስለሆነ የቦርዱ ምርጫ አስፈፃሚዎች በ (665) እና በምርጫው የምትሳተፉ መራጮች፤ ተመራጮች፤ የምርጫ ታዛቢዎች እና ሌሎችም የማህበረሰቡ ክፍሎች በ (778) እየደወላችሁ ያላቹሁን ጥያቄዎች፤ አስተያየቶች፤ቅሬታዎች እና ጥቆማዎች ለቦርዱ የጥሪ ማዕከሉ ሠራተኞች ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡