Skip to main content

በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ ለሚሳተፉ የሲቪል ማህበራት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በመራጮች ትምህርት እውቅና አሰጣጥ እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2020 በተደነገገው መሰረት በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ እውቅና የመስጠት ኃላፊነት አለበት።

በአሁኑ ወቅት ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘመውን ምርጫ በአፋር፣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቋል። በመሆኑም ቦርዱ ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ፍላጎትና ልምድ ያላቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ እውቅና ለመስጠት እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመራጮች ትምህርት እውቅና አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2020 መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  • በሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገቡ እና ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን
  • በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት በምርጫና ከምርጫ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚሠራና በሕግ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ወይም የትምህርት ተቋም
  • ከማንኛውም የፖለቲካ ግንኙነት ወይም እንቅስቃሴ ነጻ መሆን
  • የገንዘብ፤ የሰው ሃይልና ተዛማጅ ልምድን ጨምሮ ሃላፊነቶችን የመወጣት አቅም
  • በመራጮች ትምህርት እውቅና አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2020 ለመራጮች ትምህርት የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ እንዲሆኑ ይጠበቃል

የማመልከቻ ሂደቶች፡-

ፍላጎት ያላችሁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከተሉትን የማመልከቻ መመሪያዎችን በማክበር እንድታመለክቱ እናሰስባለን።

  1. በአግባቡ የተሞላና በድርጅቱ የበላይ ኃላፊ የተፈረመ የቦርዱ ማመልከቻ ቅጽ
  2. የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቅጂ
  3. የተፈረመ የማመልከቻ ደብዳቤ

ከታች በተጠቀሰው ኢሜል ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱ ሰነዶችን እንደ አንድ ፋይል በሚከተለው አድራሻ መላክ ይኖርባችኋል።

ኢሜል፡ votersedu [at] nebe.org.et

በተጨማሪ አመልካቾች የማመልከቻ ቅጾችን ከታች ባለው ሊንክ፣ ከዋና መ/ቤት እና ከክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማግኘት ይችላሉ። ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0995003865 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የማመልከቻ ቅጽ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

በተጠቀሱት ክልሎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ በመራጭ ትምህርት እና ከምርጫ ጋር በተያያዙ ተግባራት ልምድ ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና መሰል ድርጅቶች እንዲያመለክቱ በጥብቅ ይበረታታሉ።

መሳሰቢያ፡ ይህ ጥሪ በቅርቡ አመልክታችሁ እውቅና የተሰጣችሁን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አይመለከትም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post