የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው በ አፋር፤ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 ዓ.ም. በጀት ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት በ አፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በ ቤንሻንጉልጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

•ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

• ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገላችሁ

• የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆናችሁ

• የ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላችሁ

• እንዲሁም በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ መስራት የምትችሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ክፍት በሚሆነው የቦርዱን የማመልከቻ ሊንክ፡ ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም እንድታመለክቱ በትህትና እንጠይቃለን።

የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እናበረታታለን።

ማስታወቂያ
የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም