የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስነ-ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ላይ በትኩረት እየሠራ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ በትኩረት እየሠራ ሲሆን ዜጎች በቂ የስነ-ዜጋ እና ምርጫ ነክ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ቦርዱ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። በዚሁ መሠረት የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል ከቦርዱ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት አስተማሪ የሆኑ የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ቡክሌት እና ብሮሸሮችን የግንዛቤ ገለፃ በመስጠት ማሰራጨት ተችሏል።
የሥራ ክፍሉ የስነ-ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ተደራሽነትን በማስፋት ከቦርዱ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በሞጆ ከተማ በሚገኙ ሰባት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ማለትም ቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ፣ ሰዩ ስፔሻል ሁለተኛ ደረጃ፣ ሞጆ አንደኛ ደረጃ፣ ኮልባ አንደኛ ደረጃ፣ ሉሜ አንደኛ ደረጃ፣ ፋነ ሞጆ አንደኛ ደረጃ፣ ሞጆ ሁለተኛ ደረጃ እና እንዲሁም በአንድ የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማለትም ስኩል ኦፍ ኤክሰለንስ ትምህርት ቤት የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሕትመቶችን በተሳካ ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ ችሏል።
ከዚህም በተጨማሪ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኙ አስራ ሁለት ትምህርት ቤቶች ማለትም ቢሾፍቱ ሁለተኛ ደረጃ፣ ኢፈቦሩ ጨለለቃ ሁለተኛ ደረጃ፣ ቤዝባሮክ አንደኛ ደረጃ፣ ቤዝ ባሮክ ሁለተኛ ደረጃ፣ ቅዱስ ሩፋኤል አንደኛ ደረጃ፣ ኢትዮ- ፊዩቸር አንደኛ ደረጃ፣ በከልቻ አንደኛ ደረጃ፣ ሆራ አርሰዲ አንደኛ ደረጃ ፣ ከረ ሆራ አንደኛ ደረጃ፣ ጆሾዋ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ፣ ቀነኒሳ አንደኛ ደረጃ እና ኋይት ዌል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ ማሰራጨት ተችሏል ። የነገው ትውልድ ተስፋ የሆኑ ወጣቶችን በምርጫ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል::
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ