Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ድምጽ የመስጠት ሂደት እየተካሄደ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ድምጽ የመስጠት ሂደት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ቦርዱ በተለያዩ የመርጫ ጣቢያዎች ላይ እያደረገ ባለው ክትትል በወላይታ ዞን፣ በበሌ የምርጫ ማዕከል፣ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አረጋግጧል፡፡ ይህም በዞኑ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ድምፅ በመስጠት ሂደት ወቅት የቀበሌ አስተዳደር ሀላፊዎች ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ብዛት 105 የሚሆን የግለሰብ ጊዜያዊ መታወቂያዎችን በመያዝ ድምፅ ለመስጠት ለተሰለፋ ዜጎች በማደል ህገ ወጥ ተግባር ላይ በመሰማራታቸው ቦርዱ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመው የህግ ጥሰት እስኪጣራ ድረስ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወስኗል፡፡ በቀጣይም ቦርዱ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ክትትል የሚያደርግ ሲሆን ተከስተው ሲገኙ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Share this post