Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢ. ብ. አ. ፓ) ነሐሴ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ቦርዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢ. ብ. አ. ፓ) ነሐሴ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ያሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግልጽ ያልሆኑ፣ መካተት ኖሮባቸው ያልተካተቱ አንቀጾችን የለየ ሲሆን፣ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ጋር የሚቃረኑ አንቀጾች ተፈጻሚ እንዳይሆኑና ጠቅላላ ጉባዔው በቀጣይ ስብሰባው አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርጎባቸው ሪፖርት እንዲያቀርብ ቦርዱ ወሥኗል። ከላይ የተጠየቁ ማስተካከያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፓርቲው ነሐሴ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ እና የተላለፉ ውሣኔዎችን ቦርዱ የመዘገበ መሆኑን ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ደብዳቤ እዚህ ላይ ያገኙታል

Share this post