የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።
በውሣኔውም ፓርቲው ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያሻሻለው መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ጋር የሚቃረኑ አንቀጾችን የለየ ሲሆን፤ አንቀጾቹ ተፈጻሚ እንዳይሆኑ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔው በቀጣይ ስብሰባው አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርጎባቸው ሪፖርት እንዲያቀርብ ሲል መወሠኑን ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ደብዳቤዉ እዚህ ላይ ያገኙታል።
ታህሣሥ 9 ቀን 2015 ዓ.ም.