የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ዲራሼ) በአንድ ክልል መደራጀታቸውን አልደግፍም ለሚለው የሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ሃሣብ ነጭ ላም ምልክት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ይሁንና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለቦርዱ የዚህ ሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ምልክት ነጭ ላም መሆኑ ቀርቶ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መስተዳድር ዐርማ የሆነው ጎጆ ቤት እንዲሆን ጥያቄ በማቅረቡ፤ ቦርዱም የምክር ቤቱን ጥያቄ ተቀብሎ ከላይ የተጠቀሱትን ስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል መደራጀታቸውን አልደግፍም ለሚለው የሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ሃሣብ ምልክት ጎጆ ቤት እንዲሆን መወሠኑን ያሳውቃል፡፡
ታህሣሥ 7 ቀን 2015 ዓ.ም.