Skip to main content

የሕዝበ ውሳኔው ጥያቄ እና ምልክቶች ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና በ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ጥያቄ በተመለከተ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ ምልክቶችን የማስመረጥም ሂደት አከናውኗል፡፡

የሕዝበ ውሣኔው ጥያቄ አማራጮች፡-

1. “የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና 5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን እደግፋለሁ” የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምልክት ነጭ እርግብ በአስተዳደር ምክር ቤቶቹ ተመርጧል፡፡

dfgdf

2. “የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና 5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን አልደግፍም” የሚለው ተመርጧል፡፡ ለዚህ ጥያቄ አማራጭ ምልክት እንዲመርጡ ሕዝበ ውሳኔውን በመቃወም እንከራከራለን በማለት ለቦርድ ጥያቄ በጽሁፍ ያቀረቡትን 6 የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ አማራጭ ምልክት እንዲመርጡ ቢጠይቅም ፓርቲዎቹ አማራጭ ምልክት ለመምረጥ እንደማይፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ስለሆነም ቦርዱ ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን አንፈልግም ለሚለው ጥያቄ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከተዘጋጁት የምልክት ስብስቦች ነጭ ላምን በምልክትነት ጥቅም ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

ghg

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post