የቡሌ ምርጫ ክልል የድጋሚ ምርጫን በተመለከተ የተሰጠ ውሣኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እና መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሁለት ዙር ማከናወኑ ይታወቃል። ቦርዱ በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄዱባቸው የተወሠኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅቶች ሥራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ቀደም ሲል ቦርዱ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ካካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች አንዱ በሆነው በቡሌ ምርጫ ክልል የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መጠነ ሰፊ የሕግ ጥሰት እንደነበር በማረጋገጡ ምርጫው በድጋሚ እንዲከናወን ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. መወሠኑ ይታወቃል። ይህንንም የድጋሜ ምርጫ በተያዘው ዓመት በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ከሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጋር በአንድ መርኅ ግብር ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. አብሮ እንዲከናወን ቦርዱ ኅዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም. ወሥኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ኅዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም.