የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት በቦርዱ ፈቃድ የተሰጣቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 124 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መራጮች በቂ ምርጫ ነክ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ሥልት በመቀየስና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ይሰጣል። ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የትምህርት ተቋማት፤ የማስተማር ፈቃድ ይሰጣል። በዚህም መሠረት ቦርዱ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም በጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዮ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ አሌ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ለሚፈልጉ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ በጥሪውም መሠረት ቦርዱ መሥፈርቱን አሟልተው ለቀረቡ 16 የመጀመሪያ ዙር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ሰጥቷል።
1. ኮሚዩኒቲ ሰስተይነብል ዴቬሎፕሜንት ኤይድ
2. ኮንሰርን ፎር ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት
3. ፊዉቸር ጄኔሬሽን ሆፕ ፎር ቨልነረብል ችልድረን ኦርጋናይዜሽን
4. ሻይኒ ደይ ሶሻል ሰርቪስስ ኦርጋናይዜሽን
5. የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መም/ማኅበር ጽ/ቤት
6. ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
7. ሁሉን ዐቀፍ ራዕይ ለዲሞከራሲያዊት ኢትዮጵያ
8. መሽሩም ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናየዜሽን
9. ቪዥን ኒው ላይፍ ዴቬሎፕመንት
10. ሆፕፉል ጄኔሬሽን ፎር ዴቬሎፐመንት
11. ስታንድ ፎር ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት
12. ጥረት ኮሚዩኒቲ ኢምፓወርመንት ፎር ቼንጅ አሶሴሽን
13. ቪዥን ኢትዮጵያን ኮንግሬስ ፎር ዴሞከራሲ
14. ደላሳል ኮሙኒቲ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
15. የደቡብ ኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ጥምረት
16. ድሬ የተቀናጀ የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት