Skip to main content

በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖሊቲካ ፓርቲዎች እና የምርጫ ሥነ ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ቦርዱን ባቋቋመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ምርጫውን ለመዘገብ ለሚፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ ለመስጠት እና ለመከታተል የሚያስችለውን መመሪያ አርቅቆ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ ምግባር እና አሠራር መመሪያ ቁጥር 02 /2013 አፅድቋል።

የመገናኛ ብዙኃን ሕዝበ ውሣኔውን በተመለከተ ሽፋን መስጠታቸው መራጮች መረጃ እንዲደርሳቸው ከማስቻል እንዲሁም የህዝበ ውሳኔው ሂደት ግልፅ እና ትክክለኛ መሆን አለመሆኑን ተከታትሎ ይፋ ከማድረግ አንፃር የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ቦርዱ የመገናኛ ብዙኃን በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ለመዘገብ የሚያስችል የፍቃድ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ ለሀገር በቀል እንዲሁም ለዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን የዘገባ ፍቃድ ዕውቅና መስጠት ይፈልጋል።

በመሆኑም በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን፤ ለማመልከት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን እና አስፈላጊዎቹን ሠነዶች በማሟላት በቦርዱ ዋና ጽሕፈት ቤት በግንባር በመገኘት እስከ ታኅሣሥ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

መመዝገቢያ ሲስተሙን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

ጥያቄ ካልዎት contact [at] nebe.org.et ወይም በስልክ ቁጥር +251905053051 ሊያገኙን ይችላሉ።

Share this post