የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእነ ዶክተር አዲሱ መኮንን አማካኝነት ገቢ በሆነ ደብዳቤ «አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (ፍትህ)» በሚል ስያሜ በክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ለመመዝገብ የዕውቅና ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፤ ቦርዱም የቀረቡትን ሠነዶች በሕጉ መሠረት በመመርመር ያልተሟሉ ሠነዶች እንዲሟሉና መስተካከል ያለባቸውም እንዲሁ እንዲስተካከሉ በማድረግ፤ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተሰጠው የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት መሠረት «አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (ፍትህ)»ን የክልል የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ሰጥቶቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም.