የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት መስጠት ጀመረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ ሠራተኞች፤ ማለትም የዞን አስተባባሪዎች፣ ምክትል የዞን አስተባባሪዎች፣ የምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዳታ ኢንኮደሮችና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች ለነበራቸው ተሣትፎ ቦርዱ እያመሰገነ፤ በምርጫው ላይ የነበራቸውን ተሣትፎ የሚያረጋግጠውን የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ፖርታል አዘጋጅቶ አቅርቧል። የምስክር ወረቀቱ የሚመለከታቸው ሠራተኞችም የምስክር ወረቀት ፖርታሉ ላይ የሚጠየቁትን መረጃዎች በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውስድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል።