1. የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ነፍሰጡሮችን፣ ጨቅላ ህጻናት የያዙ ወላጆችን፣ መለዮ የለበሱ የመከላከያና የፖሊስ አባላትን ቅድሚያ በመስጠት ድምፅ እንዲሰጡ ማድረግ አለበት
2. በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ምልክት ለማድረግና የድምፅ መስጫ ወረቀቱን ወደሳጥን ለመክተት እገዛ የሚያስፈልገው መራጭ ራሱ የመረጠውን ሰው ይዞ የመምጣት መብት አለው
3. በዚህም መሰረት በድጋፍ ፈላጊው የሚመረጥ ሰው :-
ሀ) ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
ለ) እጩ ተወዳዳሪ ወይም የእጩ ወኪል መሆን የለበትም
4. አንድ ድጋፍ የሚሰጥ ሰው ከአንድ በላይ መራጭ ለመደገፍ አይችልም
5. ድጋፍ የሚያስፈልገው መራጭ ራሱ የመረጠውን ሰው ይዞ ያልመጣ እንደሆነ ምልክት ለማድረግ እንዲሁም የድምፅ መስጫ ወረቀት ወደ ሳጥን
ለመክተት አስፈላጊ የሆነውን ድጋፍ የሚሰጠው የምርጫ ጣቢያ ሃላፊው ብቻ ነው
ማስታወቂያ
ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም