Skip to main content

ለ2013 ጠቅላላ ምርጫ አዲስ የታዛቢነት ፈቃድ ለሚጠይቁ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበራት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ «የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011» እንዲሁም «የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012» በሚደነግገው መሠረት፣ ምርጫ ለመታዘብ ፍላጎት ያላቸውን የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይፋዊ ማስታወቂያ በማውጣትና በመመልመል በአንደኛ ዙር ለ36 ድርጅቶችን እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛ ጠቅላላ ምርጫን መታዘብ እንዲችሉ በመጀመሪያ ዙር አመልክተው ካልተመረጡ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል ለቦርዱ ይግባኝ በማስገባት ይግባኛቸው በቦርዱ ታይቶ ውሣኔ ከተሰጠባቸው እና በሁለተኛ ዙር እንደ አዲስ 6ኛ ጠቅላላ ምርጫን ለመታዘብ ማመልከቻ ካስገቡ ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት ዘጠኝ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መታዘብ እንዲችሉ ፍቃድ የሰጣቸው መሆኑን እናሳውቃለን።

ማህበራቱም

  1. ማኅበረ ሕይወት ኢትዮጵያ - ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት
  2. አልቢር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን
  3. ዲጂታል ሮግ ሶሳይቲ ኤክስፐርመንት ግሩፕ
  4. ስፕሪድ የማኅበራዊ ችግሮች መፍቻ እና የልማት ድርጅት
  5. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር
  6. ሰኔ 16 የሰላምና የለዉጥ ተምሳሌት የሲቪክ ማኅበር
  7. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
  8. የአፍሪካ ልማትና ጥበቃ ተቋም
  9. ሶሳይቲ ፎር ኢኮ ቱሪዝም ኤንድ ባዮ ዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ድርጅቶች አዲስ የምርጫ መታዘብ ፈቃድን የሚጠይቅ ማመልከቻ ለቦርዱ እያስገቡ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን፤ ምርጫ የሚደረግበትም ጊዜ እየተቃረበ በመምጣቱ፣ ካለው በጣም የተጣበበ ጊዜ አንጻር ለቦርዱም ሆነ ለማህበራቱ ተገቢውን የዝግጅት ሥራ ለመከወን አዳጋች በመሆኑ ምክንያት፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቀርቡ የመታዘብ ሥራ ጥያቄዎችን ቦርዱ መቀበል ማቆሙን በአክብሮት እናሳውቃለን!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post