በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በትላንትናው እለት በተጻፈ ደብዳቤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋር እና በሶማሌ ክልላዊ መንግስታት መሀከል ላለው የአስተዳደር ወሰን አለመግባባት ብሎም በሁለቱ ማህበረሰቦች መሀከል በየወቅቱ ለሚያገረሽ ግጭት መነሻ በሆኑ ቀበሌዎች ስር የታቀፉ ጣቢያዎች ተከፍተው የምርጫ ሂደት እንዳይደረግባቸው የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም እንደማይቀበለው በደብዳቤ ለቦርዱ ከማሳወቁም በላይ ቦርዱ “ውሳኔውን እንደገና አይቶ ካልለወጠም በምርጫው ለመሳተፍ እንቸገራለን” ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደረሰውን ደብዳቤ በተመለከተ በዛሬው እለት የሚከተለውን ምላሽ ለክልል መስተዳድሩ መስጠቱን ያሳውቃል።