የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአውሮፓ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም. የአውሮፓ ሕብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ 12 ሃርድ ቶፕ እና 10 ፒክ አፕ መኪኖችን ያካተተ ነው። ዋና ሰብሳቢዋ ቦርዱ የሎጀስቲክ እንቅስቃሴ ላይ ያለበትን ውስንነት ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ ያላቸውን ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። ቦርዱ በመንግሥትም ሆነ በአውሮፓ ሕብረት የሚደረጉለት ድጋፎች አስፈላጊነት ገልጸው፤ ለዛም ቦርዱ አመስጋኝ ነው ብለዋል።