አጭር መረጃ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ የነበረው ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል ከማሳየቱም በላይ መራጮች በተለይ የምዝገባው ማጠናቀቂያ ቀናት ሲቃረቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተመዘገቡ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖርያ ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍ፣ የመራጮች ፍላጎት እና የምርጫ ጣቢያዎች አለመመጣጠን ተስተውሏል በመሆኑም ካለፈው ሳምንት አንስቶ ቦርዱ በልዩ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት እየሰራ ይህንን ተከትሎ የሚወስዳቸውን እርምጃዎቹን የሚያሳውቅ ይሆናል። በመሆኑም ለተፈጠረው የዜጎች መጉላላት ከፍተኛ ይቅርታ እየጠየቅን እርምጃዎቹን እስኪያሳውቅ ዜጎች እና አስፈጻሚዎች በትእግስት እንዲጠብቁን እናሳውቃለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ