የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል
በመላው አገሪቱ በ11 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል, በሲዳማ ክልል እንዲሁም ሶማሌ ክልል የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ ድምጽ መስጫ ካርድ ያልወሰዳችሁ ዜጎች እንድትወስዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለዜጎች መረጃ የምታቀርቡ ሚዲያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና የፓለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የምዝገባ የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ ዜጎች ካርዳቸውን እንዲወስዱ እንድታበረታቱ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም