የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመከናወን ላይ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅና ተያያዥ የሥራ ሂደቶችን አስመልክቶ ቦርዱ በነገው ዕለት ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ በልዩ ሁኔታ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የኦፕሬሽን ሥራዎችን ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ዛሬ ላይ መድርሱ ይታወቃል።
በጊዜ ሠሌዳው ላይ በተመለከተው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅና ተያያዥ የሥራ ሂደቶችን አስመልክቶ ቦርዱ በነገው ዕለት ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ባንቢስ ሱፐር ማርኬት ዐለፍ ብሎ በሚገኘው ዲ-ሊኦፖል ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
- የሚሠሩበትን ሚዲያ መታወቂያ ወይም የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ይዞ ለመዘገብ መምጣት፣
- ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም