Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ተጨማሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰአት ድልድል አደረጉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. መሆኑን ተከትሎ ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ተጨማሪ የቅስቀሳ የአየር ሰአት ድልድል ዛሬ አከናውነዋል። በዚህም መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን እስከ ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ማከናወን የሚችሉ ሲሆን ከሰኔ 10-13 ድረስ ምንም አይነት ቅስቀሳ የማይደረግበት የፀጥታ ጊዜ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን የአየር ሰአት ድልድሉም እስከ ሰኔ 09 ድረስ የሚቆይ ነው። ፓለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪውን የአየር ሰአት ድልድል ሰነድ ከቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የስራ ክፍል በግንባር በመምጣት መውሰድ ወይም media [at] nebe.org .et ኢሜይል አድራሻ ላይ ጥያቄ በማቅረብ በሶፍት ኮፒ ማግኘት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post