መልስ - ቦርዱ የኮቪድ19 በምርጫ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡ ያደረገው ምክክር በሁለት ዙር ሲሆን በእለቱም ፓለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የሰጧቸው አስተያየቶችም ችግሩን አለም አቀፍነት በተለይ ደሞ እንደኢትዮጵያ ላለ አገር ሊያስክተል የሚችለውን ቀውስ እና በምርጫ ስራ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ እንደሚረዱ ገልጸዋል፤ ምርጫ ቦርዱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመመካከር እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ ምክክሩን ማድረጉን አድንቀው መንግስት ያስቀመጠው የ14 ቀን ክልከላ ታይቶ ቢወሰን የሚል አማራጭም አቅርበዋል፡፡ ውይይቱ በመግባባት የተጠናቀቀ ሲሆን የፓርቲ አመራሮች ይህንን እድል የአገራችንን ፓለቲካ ለማስተካከልም ሆነ በቂ ዝግጅት ለማድረግ መጠቀም እንደሚገባ፣ ይህ ውሳኔ በቦርዱ መወሰን እንዳለበት እና ፓርቲዎችን ማማከር ጥሩ ቢሆንም ውሳኔው ከፓርቲዎች በላይ መሆኑን እና በአገር የመጣ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ለመቋቋምም ሁሉም ፓርቲዎች ተባብረው መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ቦርዱ የተለያዩ ተጨማሪ ምክክሮችን ለማድረግ ያሰበ ቢሆንም
- የመጀመሪያው ውይይት የተካሄደው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በተገኘ 3ተኛው ቀን በመሆኑ ከዚያ በኋላ ያሉ ክልከላዎች መጠናከራቸው እና የተለያዩ እርምጃዎች በክልሎችም ጭምር በመወሰዳቸው ክልከላዎችን መጣስ ስለማይቻል፣ እንዲሁም ኮቪድ19 የደቀነው አደጋ በጣም ግልጽ መሆኑን ፓርቲዎችም እንደሚረዱ በማመኑ 
- ከፓርቲዎች የተገኘው ግብአት በቂ በመሆኑ እና ቦርዱም ለውሳኔው እንደግብአት ስለተጠቀመበት ቦርዱ በመግለጫው እንዳሳወቀው ውሳኔውን በሚወስንበት ወቅት የፓርቲዎችን አስተያየት እንደግብአት ከተጠቀመባቸው መረጃዎች አንዱ ነው፡፡ 

3