የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ) የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃድ አበል ክፍያ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ለማሰራት ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል ነገር ግን በቂ የሆኑ አመልካቾች ስላልተገኙ ይህንን ማስታወቂያ በድጋሚ ለማውጣት ተገዷል፡፡
የስራው ሁኔታ- የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ
የሚፈለገው ሰው ብዛት - 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ) የማመልከቻ ጊዜ- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈላጊው ቁጥር እስከሚሟላ ድረስ የማመልከቻ ቦታ- ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የምርጫ ቦርድ ማሰልጠኛ ማእከል አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
• እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
• የስራ ልምድ አይጠይቅም- ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ የቀን አበል የሚከፍል እና ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስፈጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ