የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 6000 የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃደኝነት ለአንድ ወር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን ና ኮፒ በመያዝ ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በአካል በመገኘት ከመስከረም 24 ቀን 2012 ጀምሮ በስራ ሰአት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
• እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
• የስራ ልምድ አይጠይቅም, ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ አበል የሚከፍል ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወሻ 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የላይ የተቀመጠውን ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለሶስት ተከታታይ ቀናት ያስነገረ ሲሆን ለመስማት እድሉ ያልገጠማቸውን ለመድረስ ሲባል በድጋሚ እዚህ አጋርቶታል፡፡
 

የስራ ማስታወቂያ
መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም.