Skip to main content

የኢትዯጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህትመት ውጤቶችን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት አስረከበ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ስራ ክፍል ዜጎች በምርጫ ሒደት እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤን ያገኙ ዘንድ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ትምህርቶች እና መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ላይ እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሰረት የስራ ክፍሉ በቦርዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኩል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ ሆሣዕና ከተማ አሰተዳደር፣ ሀላባ ዞን፣ ሀድያ ዞን፣ ጉራጌ ዞን፣ ስልጤ ዞን እና፣ ከምባታ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 30 የሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ትምህርት ቤቶች በአማርኛ ቋንቋ “ምርጫ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጁ በቁጥር 900 ቡክሌቶችን አስረክቧል።

ቦርዱ ዜጎች በተለይም የወደፊት መራጮች እና ተመራጮች የሚሆኑ ተማሪዎች በ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫን እንዲያደርጉ እና አጠቃላይ ስለ ሒደቱ ከወዲሁ ግንዛቤን እንዲጨብጡ ያግዝ ዘንድ በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት እሳቤ ዙሪያ የተዘጋጁ የህትመት ውጤቶችን ከቅርጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ እየሰራ መሆኑ ዜጎች በምርጫ ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የሚኖረው አስተዋጽዖ ጉልህ በመሆኑ ይህን መሰል ተግባር ለወደፈትም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

Share this post