Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን በሐረር ከተማና በአጎራባች የገጠር ከተሞች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት አሰራጨ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ ዜጋና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እና በዜጎች ተሳትፎ ዙሪያ የዜጎችን ግንዛቤ የሚያጎለብቱ መልእክቶችን የያዙ የህትመት ውጤቶችን ማዘጋጀትና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ ነው። በዚህም መሰረት የሥራ ክፍሉ ከቦርዱ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጁ በቁጥር 2950 ቡክሌቶችን እንዲሁም 46 የብሬል ቡክሌቶችን በሐረር ከተማ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች፣ ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት፣ በአጎራባች የገጠር ወረዳ ለሚገኙ ት/ት ቤቶች እንዲሁም ለአንድ መስማትና ማየት የተሳናቸው ት/ቤት አሰራጭቷል።

የቦርዱ የስነ ዜጋና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል እነዚህን መሰል የህትመት ውጤቶችን ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን ባካተተ መልኩ በማዘጋጀት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስለዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት በቂ ግንዛቤ አግኝቶ በምርጫ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ በትጋት እየሠራ ይገኛል።

Share this post