የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለየያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የስነ ዜጋና መራጮች ትምህርት ይዘት ያላቸው የህትመት ውጤቶችን አሰራጨ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል መራጮች በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ እንዲያካሂዱ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሂደት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ የህትመት ውጤቶች በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት እያሰራጨ ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል። በዚህም ሂደት የሥራ ክፍሉ ከቦርዱ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጁ በቁጥር 2160 የሚሆኑ በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ዙሪያ ያተኮሩ ብሮሸሮች፣ ቡክሌቶች፣ አዋጆች እንዲሁም የቦርዱ መልዕክት የታተመባቸው ቲሸርቶችን በኦሮሚያ ክልል በባቱና ሻሸመኔ ከተሞች በሚገኙ 18 ትምህርት ቤቶች ማሰራጨት ችሏል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የሥራ ክፍሉ በ2016 ዓ.ም. እና በ2017 ሁለተኛ ሩብ ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ 51 ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው 10,180 የህትመት ውጤቶችን ማሰራጨቱ ይታወሳል።