Skip to main content

የኢትዮጵያ ሕፃናት ፓርላማ ምርጫ ሪፖርት

ዓለም አቀፍ የልጆች ቀን ለታዳጊ ትውልድ የተሻለና አስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስፈልገውን ትምህርት የማግኘት፣ ከጤና ጥበቃ እንዲሁም ሕጻናቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እና መብቶች ጋር በተያያዘ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዳ መድረክ ሆኖ ያገለግላል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የልጆች ቀን ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ከተከበረባቸው ኩነቶች አንዱ የኢትዮጵያ ሕፃናትን ፓርላማን ምርጫ ማከናወን ነበር።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕፃናት ፓርላማም በዕለቱ ካከናወናቸው ኩነቶች ውስጥ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ 12 ክልሎች እና 2 ከተማ መስተዳደሮች ውስጥ ከተውጣጡ 154 ታዳጊዎች 14 እጩዎች በየሁለት ዓመቱ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ሕፃናት ፓርላማ ምርጫ የቀረቡ ሲሆን ፓርላማው ውስጥ ላሉት 3 የሥልጣን ዕርከኖች ማለትም የፓርላማው አፈጉባኤ፤ ምክትል አፈጉባኤ እንዲሁም ለጸሀፊነት ምርጫ ተከናውኗል። በዚህም መሰረት በ 148 ታዳጊ ሕጻናት ድምጽ ሰጭነት ምርጫው ተከናውኗል። ቦርዱ በተደረገለት የድጋፍ ጥሪ መሰረት ለምርጫ የሚሆኑ ቀሳቁሶችን በማቅረብ፤ከምርጫው በፊት ሥልጠና በመስጠት፤ ምርጫውን እስከ ፍጻሜው ድረስ በማስተባበር እና የምርጫ ሂደቱን አካሄድ ድጋፍ በማድረግ የአመራረጥ ሂደቱን እንዲሁም ውጤት በማዳመር እና በማሳወቅ ለሕጻናት ፓርላማ ምርጫ መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍ ሰጥቷል።

Share this post