1. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠውን መሠረት በማድረግ በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ማቋቋሚያ ህጉም “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011” ተብሎ ይጠራል፡፡ አዋጁ የተሻሻለው የኢትዮጵያ ምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ላይ የነበሩ የምርጫ አስፈጻሚ ተቋሙን አመሰራረትና ኃላፊነቶች ድንጋጌዎችን በመሻር መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ የተሻሻለበት ዓላማ የዜጎችን እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ከማንኛውም አካል ነፃ በሆነ የምርጫ አስፈፃሚ ተቋም እንዲመራ፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን አመላመልና አሿሿም ግልጽ ለማድረግ እና በተወዳዳሪ ድርጅቶች እና በመራጮች ዘንድ ያለውን ተአማኒነት እና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ እንዲረዳ ነው፡፡ የማቋቋሚያ አዋጁ ስለቦርዱ ሥልጣንና ተግባር፣ ስለቦርድ አባላት አሰያየም እና ሥነ ምግባር የሚደነግጉ ዝርዝር ክፍሎችን ይዟል፡፡

አዋጅ ቁጥር 1133/2011 ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ (PDFየብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ)

2. የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011

ምርጫን ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን እና ተያያዥ ሥነ ምግባርን የሚገዛው ግ “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011” ተብሎ ይጠራል፡፡ አዋጁ ስት ቀደም ሲል የነበሩ የተለያዩ ህጎችን ማለትም የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999፣ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 እና የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 662/2002 በመሻር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ የተሻሻለበት ላማ ምርጫ ሁሉን አቀፍ፣ ነፃ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ፣ የለም አቀፍ የምርጫ መርሆችን አካቶ እንዲይዝ ለማስቻል፣ ዜጎች በቀጥታና በነፃነት በመረጧቸው ተወካዮች እራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ስልጣናቸውን በተግባር ላይ ለማዋል፣ ፓለቲካ ፓርቲዎች የፓርቲ ፕሮግራምና ላማቸውን ማራመድ እንዲችሉ፣ ዜጎችና ፓርቲዎች በምርጫ ርዓት ውስጥ የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ ለመደንገግ እና ለምርጫ ሂደት ለሚነሱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ እና የዳኝነት መፍትሄ የሚሰጡ ተቋማትን እና አሰራራቸውን ለመወሰን ነው፡፡ የምርጫ ህጉ በዋናነት ስለ ምርጫ ደንብና መርህ፣ ስለፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ስለምርጫ ታዛቢዎችና የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ፤ በምርጫ ስለሚነሱ አቤቱታዎች እና ክርክሮች እና ስለምርጫ ሥነ ምግባር የሚተነትኑ ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል፡፡

አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ (PDF የኢትዮጵያ የምርጫ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ 1162)

3. በአዲሱ የምርጫ የፖለቲካ ምዝገባ እና የሥነ ምግባር ህግ የተለወጡ ዋና ዋና ጉዳዮች

በአዲሱ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የሥነ ምግባር ህግ ከቀድሞው ህግ በተለየ መሠረታዊ የሆኑ እና ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበሩ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት በህጉ ላይ የተቀየሩትን ዋና ዋና ይዘቶች ለማየት ከስር የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ  በመጫን ይመልከቱ (PDFበረቂቅ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚመለከተው ክፍል ከተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች ዋናዎቹ)

4. 6ተኛ አጠቃላይ ምርጫን መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙሃን የቀረቡ አስፈላጊ ሰነዶች

PDFየመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 02 /2013

PDFምርጫን ለመዘገብ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የመገናኛ ብዙሃን የማመልከቻ ቅፅ - Media Accreditation Form

PDFየመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች ለማረጋገጫ የሚጠቅም - Media Accreditation Checklist 

PDFእውቅና እንዲሰጣቸው የተጠየቁ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር - List of Journalists to be accredited

PDFየምርጫውን ሂደት ለመዘገብ ፈቃድ እንዲሰጠው በጠየቀ የሚዲያ ተቋም የበላይ ኃላፊ የሚሞላ ቃለመሃላ

5. ደንቦችና የቃልኪዳን ሰነዶች

PDF    የምርጫ ቁሳቁስ እና ሰነዶች ርክክብ እና የማስወገድ ሂደት መመሪያ

PDF    በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እንዲሁም በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር ሥርዓት ቃል ኪዳን

PDF    የፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለማስፈጸም የወጣ የሥነ ሥርዓት ደንብ

PDF    በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ሥርዓት እና ደንብ

PDF    ለዕጩዎች የተዘጋጀ ምልክት