Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያካሄደው የመራጮች ምዝገባ አጠቃላይ አኅዛዊ መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ በ3769 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ ባጠቃላይ 3,028,770 የመራጮች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 493 የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል።

አጠቃላይ የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽ 1,575,371 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 1,453,399 ሴቶች ናቸው። ከተመዘገቡት የአካል ጉዳተኞች ውስጥም እንዲሁ 296 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 197 ሴቶች ናቸው። ከላይ የተመለከቱት አኅዞች ቀደም ሲል ቦርዱ ይፋ ባደረገው ጊዜያዊ የመራጮች ቁጥር ላይ ባለመጠናቀቃቸው ያልተካተቱትን ጣቢያዎች እንዲሁም የድጋሚ ቆጠራ የተደረገባቸውን ጣቢያዎች ጭምር የያዘ ሲሆን፤ ድምር ውጤቱም በማዕከል ደረጃ የመጨረሻ የሚባለው የማረጋገጥ ሥራ የተከናወነበት ነው።

የሪፖርቱን ዝርዝር ሠንጠረዥ እዚህ ላይ ያገኙታል

Share this post