የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መረጃ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ 17 ምርጫ ክልሎች ( በአብዛኛው የክልል ምክር ቤት) ምርጫ ያልተከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ፓርቲዎች፣ የክልል መስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እና ምክክሮችን ሲያደርግ ቆይቶ፣ የሚያስፈልገውን የጸጥታ ፍላጎቶች ከተሟሉ ምርጫው ሊከናወንበት የሚችለውን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅርቧል። ከስር በሚገኘው ማስፈንጠሪያ የሚያስፈልገውን የፀጥታ ሃይል ሁኔታ፣ የዝግጅት ማጠቃለያ እና የቀረበውን የጊዜ ሰሌዳ መመልከት ይቻላል።
1. የጊዜ ሰሌዳ
2. የፀጥታ ሃይል ሁኔታ
3. የዝግጅት ማጠቃለያ