በድምጽ መስጫ ወቅት ስለሚተገበሩ መመሪያዎች በጥቂቱ
በድምጽ መስጫ ቦታ ወይም ከመግቢያው ስፍራ በሚሆኑበት ጊዜ የሚከተሉት ህጎች ሊተገብሩ ይገባል
ለፖለቲካ ፓርቲዎች
- በምርጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ ወይም ከመግቢያቸው ስፍራ መራጮቹን የሚያደናቅፍ ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድር ማንኛውንም አደናቃፊ ነገር ማድረግ አይፈቀድም
- በድምጽ መስጫ ወቅት መራጮች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ማናቸውም ተጽእኖዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው
- በድምጽ መስጫ ወቅት የምርጫ ዘመቻ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዲሁም የቅስቀሳ ቁሳቁስ ማሰራጨት እና የፓርቲዎችን ምልክት የሚያሳዩ አልባሳት መጠቀም የተከለከለ ነው
- ከምርጫው ወይም ከህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ እለቱ ቀን ሰልፎችን አይጥሩ
- መራጮች ማንን እና እንዴት እንደመረጡ የሚያመለክቱ የማህበራዊ ድህረ-ገጽ ዘመቻዎችን ማከናወን አይፈቀድም
- ወደ ድምጽ መስጫ ቦታ ለመድረስ እርዳታ ለመስጠት ሰዎችን ማነጋገር ወይም የምርጫ ቀን መሆኑን ለማስታወስ ይችላሉ ፡፡ እንዴት እንደሚመርጡ ተጽዕኖ ማድረግ የለብዎትም፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 08 ቀን 2013 ዓ.ም