Skip to main content

አጭር መረጃ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በአቶ አራርሶ ቢቂላ በተጻፈ ደብዳቤ ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባዔ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. አካሂዶ መተዳደሪያ ደንቡን ማሻሻሉን፣ የፓርቲውንም ብሔራዊ ምክር ቤት መምረጡን እንዲሁም በማግስቱ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. የድርጅቱን ብሔራዊ ምክር ቤት ተሰብስቦ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች መምረጡን ያስረዳሉ የተባሉ ሠነዶች በዛሬው እለት መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስገባ ሲሆን ቦርዱ ለወደፊት እነዚህን ሰነዶች የሚመረምር እና አስፈላጊውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ይገልጻል።

Share this post