በፓርቲዎች ዘንድ አንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተልን አጠናቆ ለህትመት ዝግጁ በማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ፓለቲካ ፓርቲዎች ከእጩዎች ጋር የተገናኙ ማንኛውንም አቤቱታዎች በአስቸኳይ ማጠናቀቅ ይኖርበታል።
በዚህም መሰረት ማንኛውም የእጩዎች ለውጥ/መተካት አቤቱታ የመሳሰሉት ያላችሁ ፓርቲዎች ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ24 ሰአት ውስጥ ለቦርዱ ዋናው ጽህፈት ቤት እንድታስገቡ እያሳሰብን የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት ከተጀመረ በሁዋላ ከእጩዎች ጋር የተገናኘ ለውጥ ማስተናገድ የማንችል መሆኑን እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
 
ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም