የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ሂደት ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማቅረቡ እና ምክክር እንደተደረገበት ይታወሳል። በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከዚህ መግለጫ ጋር ተያይዞ በሚገኘው እንዲሁም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድረገጽ እና በማህበራዊ ገጾቻችን በሚገኘው ማስፈንጠሪያ ( ሊንክ) በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይህንን የኦንላየን ምዝገባ ለተማሪዎች የማስተዋወቅ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።
የመመዝገቢያ ሊንክ - http://www.nebe.org.et/ovrs
ኦንላይን የመራጮች ምዝገባ ስርዓት መምሪያ https://drive.google.com/.../1ZH3rlNvGKgiRGbf6goB.../view...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሚያዝያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም