የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ክልል ደረጃ ምርጫ ለማስፈጸም የመለመላቸውን የምርጫ አስፈጻሚዎች ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሁለት ዙር በማቅረብ አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት መጠየቁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ከ አስር ፓርቲዎች የተሰጡ አስተያየቶችን

መርምሮ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል። ከአስሩ መካከል ሶስት ፓርቲዎች ዝርዝር አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን የቀሩት

1. የምርጫ አስፈፃሚው ገለልተኛ አይደለም እና የሌላ ፓርቲ አባል ነው በማለት የቀረቡ አቤቱታዎች ሲኖሩ ያለምንም ማስረጃ የቀረቡትን አቤቱታዎች ቦርዱ ያልተቀበለ ሲሆን፣ ለምሳሌ ግን የፓርቲ አባልነት የከፈሉ ማስረጃ የቀረበባቸውን አስፈጻሚ ከአስፈጻሚነት ሰርዟል፡፡

2. የምርጫ አስፈፃሚው የራሴ አባል ነው በማለት ማረጋገጫ ያቀረበ ፓርቲ በአቤቱታው መሰረት አባላቶቼ ናቸው ያሉት ከአስፈጻሚነት እንዲሰረዙ ተደርጓል።

3. በዞናችን ላሉት ምርጫ ክልሎች የአስፈፃሚዎች ዝርዝር አልተላከም በሚል ላቀረቡት ቅሬታ በሶስተኛው ዙር እንደሚላክ እንዲገለፅላቸው ተወስኗል።

4. የማይታወቁ አስፈፃሚዎች ናቸው በሚል ለቀረበው ቅሬታ የምርጫ ቦርድ የኦፕሬሽን ክፍል አድራሻቸውን አጣርቶ በሶስተኛው ዙር እንዲልክ እንዲደረግ ተወስኗል።

5. የስራ ፈጠራ ኮሚሽን እና ከማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን ከመጡ ዝርዝሮች ውስጥ ምልመላው መከናወን አልነበረበትም የሚል አቤቱታ የቀረበ ሲሆን ተቋማቱ የመንግስት ተቋማት በመሆናቸው ብቻ የሚመለመሉ ሰዎች ዝርዝር መካተት የለበትም የሚለውን ውሳኔ ቦርዱ አልተቀበለውም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም