Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ኦፕሬሽን ዝግጅቱን እና የፓርቲዎች ማእከልን ለፓለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት አስጎበኘ

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር አባላት ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው ጉብኝት ላይ የተገኙ ሲሆን በምስረታ ላይ ያለው የሴት ፓለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት አባላትም ተሳታፊ ነበሩ፡፡

የምርጫ ኦፕሬሽን በቀድሞ ምርጫዎች እንዴት እንደነበረ እና የመጪው ምርጫ የሚኖረውን ሂደት ለማሳያነት የተዘጋጁ ምርጫ ጣቢያዎችን እና የምርጫ ቁሳቁስ መጋዘኖችን ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ቦርዱ ለፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት እና ለሴት ፓለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት ያዘጋጀውን ለተለያዩ የቢሮ ስራ እና ስብሰባዎችን ለማከናወን የሚውል የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ለፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የሴት ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት አስረክቧል፡፡

Share this post