በምርጫ ሂደት የሚነሱ አለመግባባቶችና ክርክሮች አፈታት ላይ ለፌደራልና ለክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ሥልጠና ተሰጠ
መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.
አቶ ሰለሞን አረዳ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ ፕሮግራሙን የከፈቱ ሲሆን፤ ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና፣ የምርጫ እና የሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/11ን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።
ራኬብ አባተ የኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ፎር ኢሌክቶራል ሲስተምስ ካንትሪ ዳይሬክተር የምርጫ ዑደትን እና ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የምርጫ ዑደት እና ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 1162/11 ላይ በተሳታፊዎች የቡድን ውይይት እየተደረገ ይገኛል።