መግቢያ፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ ምርጫን እንዲያስፈጽም እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ ይህን ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ ተቋሙን በአዲስ መልክ በሚወጡ ሕጎች መሠረት እንደገና ማደራጀት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑ ታምኗል፡፡ ተቋሙን በአዲስ መልክ የማደራጀት ዋናው ዓላማ የተቋሙን ተዓማኒነት እና ብቃት ከፍ ማድረግ እንዲሁም ነፃ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆነ ምርጫ ማካሄድ እንዲቻል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አምስት የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ የሆኑ የቦርድ አመራሮች እንዲኖሩት የተደረገ ሲሆን፤ በተጨማሪም አዲሱ ሕግ ቦርዱ በአንድ ዋና ኃላፊና በአንድ ምክትል ዋና ኃላፊ የሚመራ ጽ/ቤት እንደሚኖረውም ደንግጓል ፡፡
በመሆኑም የምርጫ ቦርድ ለዚህ ኃላፊነት ብቃትና ሙያው ያለው ሰው በሙሉ ጊዜ የሥራ መመደብ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቢሮ ኃላፊ
ተጠሪነቱ፡- የጽ/ቤት ኃላፊው/ኃላፊዋ ተጠሪነቱ /ተጠሪነቷ ለቦርዱ ሊቀመንበር ነው፡፡
ዋና ዋና ተግባሮች፡-
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጭ የሥራ ዘርፍ (ፋይናንስ፣ ግዥ፣ ሰውሃይል አስተዳደር፣ ንብረት አስተዳደር) በኃላፊነት ይመራል/ትመራለች፤
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጭ ተግባራት አፈጻጸም ውጤታማ የሚያደርግ ስትራቴጂያዊ እቅድ ያወጣል/ታወጣለች፣
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጪ የስራ ዘርፍ አመታዊ እቅድ ያወጣል/ታወጣለች፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል/ትከታተላለች፤
•የድጋፍ ሰጪ ዘርፉ ሥራ አፈጻጸም ዋና ዋና ተግባራት ከቦርዱ ዋና ዋና የስራ ሃላፊነት ጋር በተቀናጀ መልኩ መከናወናቸውን ያረጋግጣል/ታረጋግጣለች፤
•ከቦርዱ ሰብሳቢ ጋር በመመካከር የቦርዱን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፤
•የቦርዱን ቃለጉባዔና ሌሎች ሰነዶች በአግባቡ ይይዛል/ትይዛለች፤
•የቦርዱን ውሣኔዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች እንዲተላለፉ ያደርጋል/ታደርጋለች፤
•ቦርዱ ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ያስተባብራል/ታስተባብራለች፤
•ስለ ጽሕፈት ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ በየጊዜው የሥራ አፈጻጸምን እና በጀትን ሪፖርት አዘጋጅቶ/አዘጋጅታ ለቦርዱ ሰብሳቢ ያቀርባል/ታቀርባለች፤
•በቦርዱ ስብሳቢ የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል/ታከናውናለች፡፡
የሚጠበቅ አጠቃላይ ብቃት ፡-
•ቦርዱ የሚመራባቸውን በነፃነት፣ በገለልተኝነት እና በፍትሐዊነት የመሥራት መርህዎች የሚያከብር/የምታከብር፤
•የዴሞክራሲ ተቋማት የአሠራር ሥርዓትና መርሆዎችን የሚያውቅ/የምታውቅ፤
•የብዝሃነት እና የአካታችነት መርሆዎችን የመተግበር ዝግጁነት ያለው/ያላት ፤
•የፌደራል የስራ ቋንቋ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጻፍና እና የመናገር ችሎታ ያለው/ያላት ተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ቋንቋ የሚያውቅ/የምታውቅ ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል፤
•በሥራ አመራር፣ በሰው ሃብት አስተዳደር፣ በፋይናንስና የግዢ ሥርዓት እና ደንብ ላይ በቂ እውቀትና ልምድ ያለው/ያላት፤
•የመንግሥት ተቋማትን የአሠራር ሥርዓት እና ትብብር የሚያውቅ/የምታውቅ ሂደቱንም ለማመቻቸት ዝግጁነት ያለው/ያላት፤
•ሃሳብን የመግለጽ ችሎታ፣ ከሰዎች ጋር ተባብሮ የመሥራት አቅም፤ አስቻይ የሥራ ግንኙነት እና አጋር የመፍጠር ክህሎት ያለው/ያላት
•መሰረታዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎት ያለው/ያላት
•ከሥራ ኃላፊነቱ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ቦርዱን የመወከልና የመደራደር በጣም ጥሩ የሆነ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•መረጃ እና ትንታኔን መሠረት ያደረገ ውሣኔ የማስተላለፍ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•በቦርዱ የስነ ምግባር መመሪያ ለመገዛት ዝግጁነት ያለው/ያላት
•አዳዲስ ሃሳቦችን የማስተናገድና ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን የመምራት ችሎታ ያለው/ያላት፣
•በሥራ ብዛት የሚኖርን ጫና ወይም ተጽዕኖ የመቋቋምና ሥራ በተሰጠ የጊዜ ገደብ ውስጥ ባልተመቻቹ ሁኔታዎች ሁሉ የመጨረስ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የማደራጀት እውቀትና ልምድ እንዲሁም በቡድን ወይም /በጋራ/ በአስተማማኝ ሁኔታ ሥራ ሠርቶ ማድረስ የሚችል/ የምትችል፣
•በሥራ አመራር፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በሎጅስቲክስ እና ሌሎች አግባብነት ባላቸው ተያያዥ ዘርፎች የማስተርስ ዲግሪ እና ቢያንስ የ12 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣
•በመንግሥት ተቋማት፣ በሲቪል ማኀበራት ወይም በዓለም አቀፍ ተቋማት የሠራ/የሠራች ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል
•በፋይናንስ፣ በሰው ኃይልና አስተዳደር እንዲሁም በሎጅስቲክስ ጠንካራ ቴክኒካል እውቀት ያለው/ያላት፤
•የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤
•መልካም ሥነምግባር ያለው/ያላት፤
•ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁነት ያለው/ያላት፤
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ከስር የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በኢሜል አድራሻ - electionsethiopia [at] gmail.com መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
አስፈላጊ ማስረጃዎች
•የትምህርት ማስረጃ፤
•የሥራ ልምድ፤
•አመልካቹ/አመልካቿ ለሥራው ተገቢነትና የሚያመለክትበትን ፍላጐት የሚገልጽ ከአንድ ገጽ ያልበለጠ መግለጫ እና ካሪኩለም ቪቴ (CV)፣
•ስለ ሥራ አፈጻጸማቸውና ስለ ሥነምግባራቸው የሚገልፁ (REFERNCE) የሁለት ሰዎች ስምና የስልክ አድራሻ፤
ደመወዝ፡- በስምምነት
የቅጥር ሁኔታ፡- በኮንትራት
ውድድር ውስጥ ለመግባት ማመልቻ ዶክመንቶች ሁሉ በአንድ ኢሜይል ተጠናቀው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

The English version of the post requirement can be found on the following link.
http://www.ethiojobs.net/…/NEBE-Chief-Operations-Officer--S… 

የስራ ማስታወቂያ
መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም.