የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን እያስፈጸመ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በድርጊት መርሃ ግብሩ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ጥቅምት 26 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም ጀምሮ ኅዳር 6 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝበ ውሳኔውም ኅዳር 1ዐ ቀን 2ዐ12 ዓ.ም ይከናወናል፡፡ ይህንን ሂደት መከታተል የሚፈልጉ እና ህጋዊ ምዝገባ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን እስከ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ከ30 ድረስ ለሥራው የሚመድቡትን ጋዜጠኛ (ቢበዛ ሁለት) ስም በጽሁፍ በማሳወቅ ፍቃድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5ዐ1 ድረስ በመምጣት ወይም የደብዳቤውን ስካን ቅጂ በቦርዱ ኢሜይል electionsethiopia [at] gmail.com በመላክ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ እናሳስባለን፡፡  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የጥሪ ማስታወቂያ
ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም.