የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርትና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አከናወነ
የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርትና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት እያከናወነ ይገኛል። የውይይቱ ዋና ዋና ዓላማዎች የመራጮች ትምህርት እና ምርጫ መታዘብ ላይ ያለውን ልምድ መዳሰስ፣ የመራጮች ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥና የሥነ ምግባር መመሪያ ላይ የተሰጡትን ግብአቶች ማስተዋወቅና ማወያየት፣ የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሰራርና ሥነ ምግባር መመሪያ ላይ ውይይት ማድረግ ናቸው።
በውይይቱ ላይ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን ጨምሮ የተለያዩ የቀድሞ ልምዶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ይህ ምክክር መድረክ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት ብቻ ካደረጋቸው ውይይት መድረኮች ሶስተኛው ነው።