ፍቅሬ ገ/ሕይወት

የቦርድ አባል


ፍቅሬ ገ/ሕይወት ከአምስቱ የቦርዱ ሥራ አመራር አባል አንዱ ሲሆኑ፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግ እንዲሁም በታሪክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በልማት ጥናት እንዲሁም በፕሮጀክት አስተዳደር ሠርተዋል።

ነሲም አሊ

የቦርድ አባል


ነሲም አሊ በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ለ10 ዓመት ገደማ በተለያዩ የፍርድ ቤት ዕርከኖች በዳኝነት በማገልገል ለሀገራቸው የፍትሕ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ተኽሊት ይመሰል

የቦርድ አባል


አቶ ተኽሊት በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ከ25 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ አላቸው፡፡ አቶ ተክሊት በነዚኽ ዓመታት የዐቃቤ ሕግ መመሪያ ኃላፊ፣ የከፍተኛ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የሠበር ሰሚ ችሎት ዋና ሰብሳቢ ዳኛ፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባል፣ እንዲሁም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡

Fikre Gebrehiwot

Board Member


Fikre Gebrehiwot is one of the members of the Management Board of the National Election Board of Ethiopia (NEBE). He has earned bachelor’s degrees in Law (LLB) and History (BED) from Addis Ababa University (AAU) and master’s degrees in Development Studies (MA) and Project Management (MA).