Skip to main content

ስለ ጥሞና ወቅት መረጃዎች

የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት ያካትታል፡፡ በጥሞና ወቅት ታዲያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፤ ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ኃላፊነቶች አሉ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች

  • የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምፅ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡
  • የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው አራት ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም ዓይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው)
  • የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም።
  • የምረጫ ቦርዱ የሚያወጣቸውንም መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡

ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት

  • የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በጥሞና ወቅት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ ዕጩዎችን አግኝተው ቃለ-መጠይቆችን መሥራት አይፈቀድላቸውም፡፡
  • የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ከምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ኃላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትነ እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡

Share this post