የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአፋር፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫዎችን ያካሂዳል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስቃንና ማረቆ የምርጫ ክልል ለሚደረገው ድጋሚ ምርጫ:

- በቀበሌ 1 ምርጫ ጣቢያ ቆሼ

- በሰሜን ቆሼ ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 1

- በቆሼ 02 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 3 እንዲሁም

-በእንሴኖ 01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 2 የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ይከናወናል።

በመራጭነት ለመመዝገብና ለመምረጥ ኢትዮጵያዊ መሆን፤ ምርጫው በሚካሄድበት አካባቢ ቢያንስ ለስድስት ወራት ነዋሪ መሆን፤ እንዲሁም 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህም በመስቃንና ማረቆ የምርጫ ክልል በተጠቀሱት ቀበሌዎች እና የምርጫ ጣቢያዎች የምትኖሩ መራጮች የቀበሌ፣ የትምህርት ቤት፣ የሠራተኛነት መታወቂያ ካርድ ፣ ፓስፖርት፤ መንጃፍቃድ፤ እና ከውትድርና የተገለሉበት ሰነድ፣ በማቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

ማስታወቂያ
ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም.