የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአፋር፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫዎችን ያካሂዳል።

በአፋር ክልል ለሚካሄደው ምርጫ በዳሎል፥ ጉሊና፥ አዲሌላ፥ ዳሊፋጌ፥ እንዲሁም ዳዌ የምርጫ ክልሎች በሙሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ሲሆን:

  • በቡሬሞዳይቱ የምርጫ ክልል፥ የዲያራ የምርጫ ጣቢያ ዲያራ 01
  • በገዋኔ የምርጫ ክልል በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች፡ የኦራፊታ ምርጫ ጣቢያ አመርፋጌ እና የቢዳ ምርጫ ጣቢያ ቢኢዳ
  • በሰሙሮቢ የምርጫ ክልል በአራት የምርጫ ጣቢያዎች፡ ፈንቲግራራ ምርጫ ጣቢያ ጉለሊ፤ የዳሌቲ ምርጫ ጣቢያ ሃሬዳሞት፤ ሰሙ ከዳቡራ ምርጫ ጣቢያ ካዱቡራ እና ቦርቲዳስ ኤና ጋሊፋጅ ምርጫ ጣቢያ ቦርተደስ
  • ከዚሁም በተጨማሪ በተላላክ የምርጫ ክልል በ24 ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ሲሆን ዝርዝሩ በምርጫ ክልሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ይገለጻል።

ስለዚህም በተጠቀሱት አካባቢ የምትኖሩ መራጮች የቀበሌ፣ የትምህርት ቤት፣ የሠራተኛነት መታወቂያ ካርድ ፣ ፓስፖርት፤ መንጃፍቃድ፤ እና ከውትድርና የተገለሉበት ሰነድ፣ በማቅረብ ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

በመራጭነት ለመመዝገብና ለመምረጥ ኢትዮጵያዊ መሆን፤ ምርጫው በሚካሄድበት አካባቢ ቢያንስ ለስድስት ወራት ነዋሪ መሆን፤ እንዲሁም 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን ያስፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

ማስታወቂያ
ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም.