የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአፋር፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫዎችን ያካሂዳል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚካሄደው ምርጫ በ ደምቤ፥ ምዥጋ፥ ሰዳል፥ ዛይ፥ ቡለን፥ ዳንጉር፥ ድባጤ፥ ወንበራ፥ ማንዱራ፥ ፓዌ፥ ጉባ፥ እና ልዩ ሽናሻ የምርጫ ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በሙሉ የሚከናወን ሲሆን ፡

• በመንጌ የምርጫ ክልል፤ በሰላማ ምርጫ ጣቢያ ሰላማ-ሀ

• በሆሞሻ የምርጫ ክልል፤ በ01 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ 01 ቀበሌ 01 ሀ2B

• በአሶሳ ሆሃ ምርጫ ጣቢያ፤ አምባ 7 ምርጫ ጣቢያ አምባ 7

• በከማሺ የምርጫ ክልል፤ በካማሺ ምርጫ ጣቢያ

• በኦዳብልግዱል ምርጫ ክልል ላይ ደግሞ በ6 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ያከናውናል።

ስለዚህም በተጠቀሱት አካባቢ የምትኖሩ መራጮች የቀበሌ፣ የትምህርት ቤት፣ የሠራተኛነት መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃፍቃድ፤ እና ከውትድርና የተገለሉበት ሰነድ፣ በማቅረብ ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

በመራጭነት ለመመዝገብና ለመምረጥ ኢትዮጵያዊ መሆን፤ ምርጫው በሚካሄድበት አካባቢ ቢያንስ ለስድስት ወራት ነዋሪ መሆን፤ እንዲሁም 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን ያስፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

ማስታወቂያ
ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም.