የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በአፋር ክልል በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣ በቡሬሞዳይቱ ፣ ገዋኔ ፤ በዳሎል እና በጉሊና የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ነዋሪ የሆኑ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

• ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

• ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገላችሁ

• የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆናችሁ

• የ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላችሁ

እንዲሁም በተጠቀሱት አካባቢዎች ነዋሪ የሆናችሁ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ክፍት በሚሆነው የቦርዱ የማመልከቻ ሊንክ በመጠቀም እንድታመለክቱ እንጠይቃለን።

የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እናበረታታለን።

የስራ ማስታወቂያ
መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም